Pair of Vintage Old School Fru
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

አስፈላጊ ትምህርቶች ለብዙሃኑ ህዝብ


✍ አዘጋጅ: ሼህ አብዱል አዚዝ ባዝ
ተርጔሚና አሳታሚ ኢስላማዊ ዳእዋና ዕውቀት ማህበር ሁለተኛ እትም ላይ የተወሰደ
Iqra በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

አንደኛ ትምህርት


ፋቲሐ(የመክፈቻይቱ) ምዕራፍ ጨምሮ ከአል-ዙልዚላህ (የእንቅጥቃጤው) ምእራፍ ጀምሮ እስከ አል-ናስ(የሰዎች) ምዕራፍ ድረስ ካሉት አጫጭር ምእራፎች የተቻለውን ያህል ንባባቸውን በማስተካከልና በቃል በማጥናት እንዲሁም ትርጉሙን ማወቅ።

ሁለተኛ ትምህርት

ከአሏህ በስተቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር፤ ይኽውም ከአንድ አሏህ በስተቀር ሊያመልኩት የሚገባ ጌታ ስላለመኖሩና ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን ከነትርጉሙ እንዲሁም የላ ኢሃ ኢለሏህን ቅድመ ሁኔታዎችን(ሹሩጦችን) ከማብራራት ጋር ማስተማር ነው። ትርጉም: «ላ ኢላሃ» የሚለው ከአሏህ ሌላ አምላክ እንደሌለ የሚያሳይ አሉታዊ ቃል ሲሆን «ኢለሏህ» የሚለው ደግሞ አምልኮ ለአንድ አሏህ ብቻ መሆኑን የሚያረጋግጥ አወንታዊ ቃል ነው።

«የላ ኢላሀ ኢለሏህ» ቅድመ ሁኔታዎች(ሹሩጦች)

እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በዚህ መንገድ መግለጽ ይቻላልል። ዕውቀት ፣ እርግጠኝነት ፣ ፍፁምነት ፣ እውነተኝነት ፣ ውዴታና መቀበል ፣ ታዛዥነት እንዲሁም ከሏህ ውጭ የሚመለኩ ነገሮችን መካድ ናቸው።

ሦስተኛ ትምህርት

የእምነት መሰረቶች ስድስት ናቸው። አነሱም፦

በአሏህ ማመን ፣ በመላዕኮቹ ፣ በመጸሐፎቹ ፣ በመልክተኞቹ ፣ በመጨረሻውቀን እና በቀደር ጥሩም ሆነ መጥፎ በአሏህ እውቀት ነው ብሎ ማመን ናቸው።

አራተኛ ትምህርት

የተውሂድ ክፍሎች(አሏህን አንድ የማድረግ ክፍሎች) ሶስት ናቸው። እነሱም፦ የጌትነት አንድነት ፣ የአምላክነት አንድነት ፣ የስሞችና የባህርያት አንድነት ናቸው።

የሽርክ የማጋራት ክፍሎችም ሦስት ናቸው። ትልቁ ማጋራት ፣ ትንሹ ማጋራትና ድብቁ ማጋራት ናቸው። ትልቁ ማጋራት የተግባር ክስረትንና በጀሃነም እሳት ውስጥ መዘውተርን ያስከትላል። አሏህ እንዲህ ብሏል፦

"ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበረ ከነሱ በታበሰ ነበር።"

{አል-ቁርአን}


"ለከሃዲዎች በነፍሶቻቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሆነው የአሏህን መስጊዶች ሊሰሩ አይገባቸውም። እነዚያ ስራዎቻቸው ተበላሹ እነሱም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው።"

{አል-ቁርአን}

በዚህም ላይ የሞተ ሰው በምንም አይነት አይማርም። ጀነትም ለሱ እርም ናት።

"አሏህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። ከዚህም ሌላ ያለውን ለሚሻ ይማራል።"

{አል-ቁርአን}


"እነሆ በአሏህ የሚያጋራ ሰው አሏህ በርሱ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያቸው እሳት ናት። በዳዮች ምንም ረዳት የላቸውም።"

{አል-ቁርአን}

በዚህ ክፍል ከሚጠቃለሉት መካከል ሙታንንና ጣኦታትን መጥራት ፣ በነሱ መመጀን ፣ መሳል ፣ ለነሱ ማድና ሌሎችም ይገኙበታል። ትንሹ ማጋራት ማለት ደግሞ በቁርአን ወይም በሐዲስ ማጋራት ሽርክ ተብሎ ተገልፆ ግን ከትልቁ የማጋራት ዓይነት ያልሆነ ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ነገር ሲፈጸም ለይዩልኝ መፈጸም ፣ ከአሏህ ሌላ ባለ ነገር መማል ፣ አሏህና እገሌ ካሉ ማለትና የመሳሰሉት ናቸው።

ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ: ለእናንተ ከምፈራላችሁ ሁሉ የምፈራው ትንሹን ማጋራት ነው ብለው ሲናገሩ፤ እሱ ምንድ ነው በማለት ተጠይቀው ሲመልሱ፦ ለይዩልኝ መስራት ነው ብለዋል። ይህ ሐዲስ በጥሩ የዘገባ ሰንሰለት ኢማሙ አህመድ ፣ ጦበራኒና በይሐቂ ሙሐመድ ብኑ ለቢድ የተባሉትን ሰሃባ ጠቅሰው ዘግበውታል። ጠበራኒና በሌላ የዘገባ ሰንሰለት እኚህ ሰሃባ ባከራዕብን ከዲጅ የሰሙትን እንደሚከተለው ዘግበውታል፦

"ከአሏህ ሌላ ባለ ነገር የማለ በእርግጥ አሏህን ካደ ወይም በአሏህ አጋራ።"

{አቡዳውድና ቲርሚዚ}


"አሏህና እገሌ ካሹ አትበሉ እንግዲያውስ አሏህ ካሻ ከዚያም እገሌ ከሻህ በሉ"

{አቡ-ዳውድ}

ሶስተኛው ክፍል ድብቁ ማጋራት ነው። ማስረጃው ተከታዩ የነቢያችን(ሰ.ዐ.ወ) ቃል ነው።

"አዋጅ! ከደጃል ይበልጥ የምፈራላችሁ ነገር ምን እንደሆነ ልንገራችሁ ሲሏቸው። እሺ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ ይንገሩን አሏቸው። ድብቁ ማጋራት ነው አሉ። እሱ ሰውየው ይቆምና ይሰግዳል፤ ሶላቱን ያሳምራል ሰውየው ወደሱ መመልከቱን ስላየ።"

{ኢማሙ አህመድ}

አምስተኛ ትምህርት

የእስልምና ማእዘናት አምስት ናቸው። እነሱም፦

  1. ከአሏህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንና ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ(ሱ.ወ.ተ) መልዕክተኛ ናቸው ብሎ በአንደበቱ መመስከር

  2. ሶላትን መስገድ

  3. ዘካን መስጠት

  4. የረመዷንን ወር መፆም

  5. መስፈርቱን ያሟላ ሰው የሐጅ ፀሎት ማድረግ

ስድስተኛ ትምህርት

የሶላት ቅድመ ዝግጅቶች(ሸርጦች) ዘጠኝ ናቸው። እነሱም፦

  1. ሙስሊም መመሆን

  2. የአእምሮ ጤናማነት

  3. ጠቃሚንና ጐጂን፤ጥሩና መጥፎውን ለይቶ የማወቅ ዕድሜ መድረስ

  4. ትልቁንና ትንሹን ሐደስ ማስወገድ

  5. ነጃሳን ነገር ማስወገድ

  6. ሃፍረተ ገላን መሸፈን

  7. የሚሰገደው የሶላት ጊዜ መግባት

  8. ፊትን ወደ ካእባ(ቂብላ) ማዞርና

  9. ኒያ ናቸው።

ትልቁ ሐደስ ማለት ሙሉ ሰውነት መታጠብ የሚያስፈልግበት ማለት ሲሆን ትንሹ ሐደስ ማለት ደግሞ ውዱእ የሚያስፈልግበት ማለት ነው።

ሰባተኛ ትምህርት

የሶላት ማዕዘናት አሥራ አራት ናቸው። እነሱም፦

በነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰላት ማውረድና በሁለቱም ጐን አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ ማለት ናቸው።

ስምንተኛ ትምህርት

የሶላት ዋጅቦች ስምንት ናቸው። እነሱም፦ ከመጀመሪያው ተክቢራ በስተቀር በሶላት ውስጥ ያሉ ተክቢራዎች በሙሉ ፣ የሚያሰግድው ሰው ኢማም ወይም ብቻውን ሰጋጅ «ሰሚአሏሁ ሊመንሃሚዳህ» (አሏህ አመስጋኙን ሰሚ ነው ማለት) የሚሰግዱት ሁሉ «ረበና ወለከል ሀምድ» ጌታችን ሆይ! ምስጋና ለአንተ ይሁን ማለት ፣ ሲያጐነብሱ(ሩኩእ ሲያደርጐ) «ሱብሀነ ረቢየል አዚም» ታላቁ ጌታ ጥራትና ልእልና ይገባው ማለት ፣ መሬት ላይ ሲደፉ(ሱጁድ) ሲያደርጉ «ሱብሐነ ረቢየል አዕላ» ሀያሉ ጌታ ጥራትና ልዕልና ይገባው ማለት ፣ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል «ረቢ ግፊርሊ» ጌታየ ማረኝ ብሎ የሚጀምረውን ፀሎት ማድረግ ፣ የመጀመሪያውን ተሸሁድና አተህያቱ ለሱም መቀመጥ ናቸው።

ዘጠንኛ ትምህርት

በሶላት ውስጥ የሚገኙ ሱናዎች

አስረኛ ትምህርት

ሶላትን የሚያበላሹ ነገሮች ስምንት ናቸው። እነሱም ሆን ብሎ ማውጋት ፣ ሳቅ ፣ መብላት ፣ መጠጣት ፣ ሐፍረተ ገላ መግለጥ ፣ ከካዕባ(ቂብላ) አቅጣጫ መዞር ፣ በሶላት ውስጥ በተከታታይ ብዙ እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ የውዱእ መበላሸት(ማፍረስ) ናቸው።

አስራ አንደኛ ትምህርት

የውዱእ ቅድመ ሁኔታዎች(ሸርጦች) አስር ናቸው። እነሱም፦ ሙስሊም መሆን ፣ የአእምሮ ጤናማነት ፣ ጠቃሚና ጐጅውን ፤ ጥሩና መጥፎውን ለይቶ የማወቅ እድሜ ላይ መድረስ ፣ መነየት ፣ ውዱእ እስኪያበቃ ላለማቇረጥ መወሰን ፣ ውዱእን የሚያስገድዱ ነገሮች መቇረጥ ፣ አስቀድሞ እስቲንጃ ማድረግ ፣ ውሃው ንፁህና ሊጠቀሙበት የተፈቀደ መሆን ፣ ውሃ ወደ ሰውነት እናዳይደረስ የሚከለክሉ ነገሮችን ማስወገድ ናቸው።

አስራ ሁለተኛ ትምህርት

የውዱእ ግዴታዎች ስድስት ናቸው። ፊትን መታጠብ፣አፍን መጉመጥመጥና ፣ በአፍንጫ ውሃን ማስገባትና ማስወጣት ፣ ሁለቱን እጆች ከክርኖች ጋር ማጠብ ፣ ሁሉን የራስ ፀጉርና ጆሮዎችንም ጭምር ማበስ ፣ ሁለቱን እግሮች እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ማጠብ ይገኙበታል።

ውዱእን የሚያበላሹ ነገሮች ስድስት ናቸው። እነሱም፦ በብልቶች የሚወጣ ቆሻሻ ፣ በእንቅልፍም ሆነ በሌላ ነገር አእምሮን መሳት ፣ ሁለቱን የእፍረት ገላ ያለምንም ከለላ በእጅ መንካት ፣ የግመል ስጋ መብላት ወ.ዘ.ተ ናቸው።

አስራ ሶስተኛ ትምህርት

ማንኛውም ሙስሊም እንዲላበሳቸው የተደነገጉ ባህሪያትና ሥነ-ምግባሮች፦ እውነተኝነት ፣ ታማኝነት ፣ ጥብቅነት ፣ እፍረት(ሐያእ) ፣ ጀግንነት ፣ አሏህ ከከለከላቸው ነገሮች ሁሉ መራቅ ፣ ጉርብትናን ማሳመር ፣ በተቻለ አቅም ችግረኞችን መርዳትና ሌሎችም በቁርአንና በሐዲስ የተደነገጉ ባህሪያቶች ይገኙበታል።

አስራ አራተኛ ትምህርት

ኢስላማዊ ስርአቶች ከነዚህም መካከል፦ ሰላምተኝነት ፣ ፈገግተኝነት ፣ በቀኝ መብላት መጠጣት ፣ ወደ መስጊድ ወይም ወደ ቤት ሲገቡና ሲወጡ ፣ መንገድ ሲሄዱ እንዲተገብሩ የተደነገጉትን ስርአቶች መጠበቅ።

አስራ አምስተኛ ትምህርት

ከሚከተሉት ወንጀሎች እንጠንቀቅ። በአሏህ ከማጋራት ፣ ከድግምት ፣ ሰውን ከመግደል ፣ የየቲሞችን ገንዘብ ከመብላት ፣ ወለድ(አራጣ) ከመብላት ፣ የወላጅ ሃቅን ከመርገጥ ፣ ዝምድናን ከማቃረጥ ፣ የሃሰት ምስክርነት ከመስጠት ፣ በሐሰት ከመማል ፣ ጐረቤቶችን ከማስቸገር ወዘተ እንጠንቀቅ!!!

አስራ ስድስተኛ ትምህርት

ስለ ኢስላማዊ ስርአቶች ከነዚህም መካከል ሰላምተኝነት ፣ ፈገግተኝነት ፣ በቀኝ መጠጣትና መብላት ፣ ወደ መስጊድ ወይም ወደ ቤት ሲገቡና ሲወጡ እንዲሁም መንገድ ሲሄዱ እንዲተገበሩ የተደነገጉትን ስርአቶች መጠበቅ ከወላጆች ጋርና ከዘመዶች ፣ ከጎረቤቶች ፣ ከአዋቂዎች እና ከህፃናቶች ጋር ሊኖር የሚገባውን ስርአት መተግበር! ህፃን ሲወለድ እንኳን ደስ አሏችሁ በማለት የደስታ መግለጫ መስጠት ፣ ሰው ለሞተበት አሏህ ትዕግስቱን ይስጥህ በማለት ማፅናናትና ሌሎች ኢስላማዊ ስርዓቶችን መጠበቅ።

አስራ ሰባተኛ ትምህርት

ከማጋራትና ከወንጀሎች ሁሉ መጠንቀቅ ነው። ከእነዚህም መካከል ሰባቱ የሰው ልጆችን አጥፊዎች በመባል የሚታወቁት ከባድ ሃጢያቶች ይገኙበታል። እነሱም በአሏህ ማጋራት ፣ ድግምት ፣ አሏህ ክልክል ያደረግልትን ነፍስ ያለ አግባብ ማጥፋት ፣ የየቲሞችን ገንዘብ መብላት ፣ አራጣ ወይም ወለድ መብላት ፣ በጅሃድ ወቅት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ፣ ንፁህ የሆነች ሴትን በዝሙት መወንጀል።

ከዚህም በተጨማሪ የወላጆችን ሐቅ መርገጥ ፣ ዝምድናን መቁረጥ ፣ በሐሰት መመስከር ፣ የሐሰት መሃላ ፣ ጎረቤትን ማስቸገር ፣ ሰዎችን በደም በገንዘብ በገመና መበደል እና ማስቸገር ሌሎችም አሏህ ወይም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የከለከሏቸው ሁሉ ነገሮች ይገኙበታል።

አስራ ስምንተኛ ትምህርት

እሬሳን መሸኘት በእሱ ላይ መስገድ ዝርዝሩ የሚከተለው ነው።

የሬሳ አዘገጃጀት፦


  1. መሞቱ ሲረጋገጥ አይኖቹ ይገጠማሉ መንጋጭላዎቹ ይገጠማሉ።
  2. እሬሳው ሲታጠብ እፍረተ ገላው ይሸፈናል። ቀጥሎም ትንሽ ከፍ ይደረግና የሚወጣ ነገር ካለ ይወጣለት ዘንድ ሆዱ በቀስታ ይጨመቃል። ከዚያ ቀጥሎ አጣቢው በእጁ ላይ ጨርቅ መሳይ ነገር ጠቅልሎ ኢስቲንጃ ያደርግለታል። ከዚያም የሶላት ውዱኡን የመሰለ ያደርግለታል። ቀጥሎም እራሱንና ፂሙ በውሃና በቁርቁራ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ነገር ያጥበዋል ከዚያ ቀኝ ጎኑን ያጥባል። አስከትሎም ግራውን እንደዚሁ እያደረገ ለሁለተኛና ለሶስተኛ ጊዜ ያጥበዋል። በእያንዳንዱ እጥበት ሁሉ እጅን በሆድ ላይ ያስኬዳል (ያሸዋል) የሆነ ነገር ከወጣ ያጥበውና መውጫውን በጥጥ ወይም በሌላ ነገር ይወትፈው። ይህም ካልገደበው በንፁህ የአፈር ጭቃ ወይም በዘመን አመጣሽ የህክምና ዜዴ ማፈኛ ይዝጋው። ውዱእ እንደገና ያድርግለት በሶስቱ ባይፀዳ እስከ አምስት እስከ ሰባት ይጨምርለት ከዚያም በጨርቅ ያድርቀው። በመታጠፊያዎችና በሱጁድ ማድረጊያ ቦታዎች ላይ ሽቶ ያድርግለት። በመላ አካላቱ ላይ ሽቶ ቢደረግለት ይመረጣል። ከፈኑን በጭስ ያጥንለት። ሪዝና ጥፍር ረጅም ከሆኑ ይቆረጣሉ ፀጉሩ አይበጠርም፤ ሴት ግን ፀጉሯ ል3 ተጎንጉኖ ወደ ኋላዋ ይለቀቃል።

  3. እሬሳን መገነዝ
  4. ወንድ ከሆነ በሶስት ነጫጭ ጨርቆች ፣ ቀሚስና ጥምጣም በሌላቸው መገነዙ ይበልጣል። ተራ በተራ ይጠቀለልበታል። በቀሚስ በሽርጥና በአንድ ብትን መጠቅለያ ቢገነዝ ምንም አይደል። ሴት ግን በአምስት ጨርቆች ማለት በቀሚስ በጉፍታ በአንድ ሽርጥና በሁለት መጠቅለያ ጨርቆች ነው የምትገነዘው። ህፃን ልጅ ከአንድ እስከ ሶስት በሚሆኑ ጨርቆች ይገነዛል። ሴት ህፃን በቀሚስና በሁለት ጨርቆች ትገነዛለች።

    እሬሳን ለማጠብ በእሱ ላይም ለመስገድና ለማስቀበር መብት ሟቹ የተናዘዘለት ሰው ነው። ከዚያም የሟቹ አባት ፣ አያት ፣ ወራሽ ዘመዶች እንደቅርበታቸው። ሴትን ለማጠብ ባለመብት የተናዘዘችላት ስትሆን ከዚያም እናት ፣ አያት ከዚያም ሴት ዘመዶች እንደቅርበታቸው ደረጃ ባልና ሚስት አንዱ ሌላውን ሊያጥብ ይችላል። አቡ በክር ሲዲቅን ያጠቧቸው ሚስታቸው ነበሩ። አሊም ባለቤታቸው ፋጡማን አጥበዋል።

    በሟች ላይ አሰጋገድ እንደሚከተለው ነው። አራት ጊዜ አሏሁ አክበር ይባላል። ከመጀመሪያ ቀጥሎ ፋቲሃ(የመክፈቻው) ምዕራፍ ይነበባል። አብሮ ሌላ አጠር ያለ የቁርአን ምዕራፍ ወይም አንድ አንቀፅ ወይም ሁለት አንቀፅ ቢነበብ ጥሩ ነው። ይህን በተመለከተ አብዱሏሂ ኢብኑ አባስ የዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ ስላለ ነው። ሁለተኛውን ተክቢራት ካደረገ ብኋላ በሶላት በተሸሁድ ውስጥ በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሰለዋት እንደሚለምን ሁሉ የምን(ያውርድ) ሶስተኛውን ተክቢራ ካደረገ በኋላ የሚከተለው ፀሎት ይነበባል።

አሏህ ሆይ! በህይወት ያለንም የሞተንም በቅርብ ያለውንም በሩቅ ያለውንም ትልቆችንም ትንሾችንም ወንዶችንም ሴቶችንም ማረን። አሏህ ሆይ! ከመካከላችን በህይወት የምታቆየውን ሰው በኢስላም ላይ አቆየው። ከመካከላችን የምታሳርፈውን በእምነት ላይ እንደሆነ አሳርፈው። አሏህ ሆይ! ምህረት አድርግለት እዘንለትም ጠብቀው ይቅርም በለው መስተንግዶውን አሳምርለት፤ መግቢያውንም አስፋለት ሃጢያቱንም በውሃና በበረዶ እጠብለት ነጭ ልብስ ከቆሻሻ እንደሚፀዳው አፅዳው። ከቤቱ የተሻለ ቤት ከቤተሰቡ የተሻለ ቤተሰብ ቀይርለት።

ወደ ገነትም አስገባው ፤ ከቀብር ውስጥ ቅጣትና ከእሳትም ቅጣት ጠብቀው። መቃብሩንም አስፋለት፤ አብራለትም። አሏህ ሆይ! ምንዳውን አትንፈገን ከእርሱ ብኋላ እጣችነንን ጥመት አታድርግብን።

ከአራተኛው ተክቢራ በኋላ በቀኝ ጎኑ ብቻ ሰላምታ ይባላል በእያንዳንዱ ተክቢራ እጅን ማንሳቱ ይወደዳል።

ኢማሙ ለማሰገድ ሲቆም ሱናው ሟች ወንድ ከሆነ በራሱ አቅጣጫ ሴት ከሆነች በመሐከል ሰውነቷ አቅጣጫ መቆም ነው። ወንድና ሴት ከሆኑ ወንድ ወደ ኢማሙ በኩል ሴቷ ወደ ቂብላ በኩል ነው የሚደረገው። ህፃን ካለ መጀመሪያ ህፃኑ ቀጥሎ ሲቲ ቀጥሎም ህፃኗ ሆነው የሚቀመጡት። የህፃኑ ራስ በውንድ ራስ አቅጣጫ ሲሆን የሴት መሐል ሰውነት እንደዚሁ በውንዱ ራስ ትይዩ ይሆናል። እንደዚሁ የህፃኗ ራስ አቅጣጫ የሚሆነው። በሴት ራስ አቅጣጫ የህፃኗ መኸከል ከወንዱ ራስ አቅጣጫ ነው የሚሆነው የሚሰግዱት ሰዎች በሙሉ ከኢማሙ በኋላ ይሆናሉ። አንድ ሰው ብቻ ቦታ ካለገኘ በኢማሙ በቀኝ ጎን ይቆማሉ።


Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra
5125

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ